Wednesday, January 29, 2014

አምባሳደር ዘውዴ ረታ

Geez Bet | 3:55 AM | | | | | | | |

‹‹በስሚ ስሚ ከየትም የሚለቃቀሙ ታሪኮች ናቸው ችግር እየፈጠሩ ያሉት››

አምባሳደር ዘውዴ ረታ በቀዳሚዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በጋዜጠኝነትና በዲፕሎማትነት ሲታወቁ በዚህ ዘመን ደግሞ የታሪክ ተመራማሪና ጸሐፊ ናቸው፡፡
ታሪክ ሲጽፉም ማስረጃዎችን በሚገባ እንደሚያገላብጡና እንደሚመረምሩ ይነገርላቸዋል፡፡ በተለይ ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ ለንባብ ባበቋቸው የታሪክ መጻሕፍት የበለጠ ይታወቃሉ፡፡ ‹‹የኤርትራ ጉዳይ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት፣ ተፈሪ መኮንን ረጅሙ የሥልጣን ጉዞ፣ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ታሪክ›› የሚባሉት መጻሕፍት የበለጠ ታዋቂ አድርገዋቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅትን መሥርተው በኃላፊነት ከመምራታቸው በፊት፣ የቤተ መንግሥት ዘጋቢ የነበሩ ሲሆን፣ ረዳት ሚኒስትር ደረጃ ደርሰዋል፡፡ በዲፕሎማሲው ዓለም ደግሞ በተለያዩ አገሮች በተለያዩ ኃላፊነቶችና በአምባሳደርነት ጭምር አገልግለዋል፡፡ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን

የፓን አፍሪካኒዝም ራዕይ ጭንገፋ! (ክፍል ሁለት)

Geez Bet | 3:53 AM | | | | | | | | | | | | | | | | | | | |





ዚህ በፊት በጻፍሁት ጽሁፍ ስለ ፓን አፍሪካኒዝም ጅማሮ (አመሰራረት) ለማሳየት ሙከራ አድርጊያለሁ። ዛሬ ደግሞ የአፍሪካ ሕብረት እንዴት እንደተመሰረት ትንሽ ካየና በኋላ የፓን አፍሪካኒስቶች ራዕይ እንዴት በአፍሪካ አምባገነን መሪዎች እንደጨነገፈ እናያለን፡፡
    በ1960ዎቹ ብዙ የአፍሪካ ሃገራት ነጻነታቸውን ያገኙበት ነበር፡፡ እነዚህ ነጻነታቸውን የተጎናጸፉ (የተጎናጸፉ የሚለው በምጸት ይነበብልኝ) ሃገራት ዳግም በኢምፔራሊስቶች እንዳይወረሩ የአፍሪካ አንድ መሆንን በየቦታው ማቀንቀን ጀመሩ። በተለይ ኩዋሜ ንኩርማህ አፍሪካ ጠንካራ እንድትሆንና ከውጭ ተጽዕኖ እንድትላቀቅ መዋሃድ አለባት ብሎ ያምን ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የያኔዎቹ መሪዎቹ ካሁኖቹ ጋር ሲወዳደሩ እጅግ ተራመጅ ነበሩ፡፡ በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች የአፍሪካ አንድነትን (ውህደትን) የሚያቀነቅኑ ቡድኖች አጎነቆሉ። ዋና ዋናዎቹ የሚባሉት ቡድኖች የካዛብላንካና ሞኖረቪያ ናቸው፡፡ ሁለቱም ብድኖች የአፍሪካ አንድነት እንዲመሰረት ጽኑ አቋም ቢኖራቸውም፣ እንዴት ነው መመስረት ያለበት የሚለው ጥያቄ ግን የልዩነታቸው ወሰን ሆኖ

የፓን አፍሪካኒዝም ራዕይ ጭንገፋ!

Geez Bet | 3:49 AM | | | | | | | | | | | | | | | | | | | |

              ክፍል አንድ 
W. E. B. Du Bois
 ምዕራባዊያን አፍሪካን በበጎ ነገር አያነሷትም፡፡ የቀደምት ስልጣኔዋንም አምነው አይቀበሉትም፡፡ አፍሪካዊያኑም ቢሆኑ ስለማንነታቸውና ስለታሪካቸው ያላቸው እውቀት ፈረንጆች አፍሪካን ከሚያውቋት እጅግ ያነሰ ነው፡፡ ይህ ነገር ደግሞ አሁን አፍሪካ ካለባት ችግር በተጨማሪ ነገሩ የገለባ እሳት ሆኖባታል፡፡ አፍሪካ ባንድ ወቅት ኃያል ሃገር ነበረች፡፡ ነገር ግን ስልጣኔዋ ተሸመደመደና ወደ ጨለማው ዘመን ገባች፡፡ የስልጣኔ መሽመድመድ በታሪክ አፍሪካ ብቻ ሳትሆን አውሮፓንም ደቁሷታል፡፡ ምስጋና ይግባቸውና የሰሜን አፍሪካ ሙሮች (Moors) በሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወደ አውሮፓ ተሻግረው፣ ጨለማ ውስጥ የምትገኘውን አህጉር አቀኑ፡፡ ከዚያ በኋላ አውሮፓ ሰለጠነችና አፍሪካን ተቀራመተች፡፡ ይህንን የአፍሪካ ቅርምጥ የአብርሆት (Enlightenment) ዘመን ልሂቃን የሚባሉት ጭምር ደግፈውታል፡፡ የአፍሪካ ህዝብ ሰብአዊ መብቱ ተገፎ ሰው ያለመሆኑ ታወጀ እና ለባርነት ተጋዘ፣ ተገረፈ፣ ተሰቃየ፣ ተሰቀለ፣ ታደነ፣ ታነቀ፣ ተገደለ፣ ንብረቱ ተዘረፈ፣ የአገር ባለቤትነቱን ተነጠቀ፣ ሳይፈልግ የወራሪዎቹን ባህል፣ ትምህርት፣ ኃይማኖት እንዲቀበል ተገደደ ………. ምን ያልሆነው አለ? እናም ይሄንን ግፍ አሽቀንጥረው ለመጣል ሃሳብ ያላቸው ጥቁር ልሂቃን በየቦታው ማኮብኮብ ጀመሩ፡፡ በመጀመሪያ ሰለ እነዚህን ንቅናቄዎች እና ኢትዮጵያኒዝም ትንሽ እንመለከታለን፡፡ ከዚያም ወደ ፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ እና ዓላማ፣ በመጨረሻም የፓን አፍሪካኒዝም ራዕይ እንዴት በአፍሪካዊያን አምባገነን መሪዎች እንደጨነገፈ

Powered by Blogger | © Copyright 2014 www.geezbet.com | Designed By Geez Bet = If you need such type blog, call on 09 1919 3131